ተቋማዊ የባህል ግንባታ ለአንድ ተቋም ራዕይ ተልዕኮ እና ግቦች መሳካት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና በፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ለፍትህ ቢሮ ሰራተኞች ተቋማዊ ባህል ግንባታ እና በስራ ስነ-ምግባር ዙሪያ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ተቋማዊ የባህል ግንባታ ለአንድ ተቋም ራዕይ ተልዕኮ እና ግቦች መሳካት ሚናው የጎላ መሆኑ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ናቸው፡፡ በመድረኩ ተቋማዊ ባህል ግንባታ እና በስራ ስነ-ምግባር ጠቀሜታ ተያያዥ ሀሳቦች ላይ ማለትም ስለ ስነ-ምግባር ምንነት፣ ስለ ስነ-ምግባር ምንጮች/ መሰረቶች፣ ስለ ስራና ሙያ ምንነት፣ ስለ ስራና ሙያ ስነ-ምግባርና ፋይዳው/ጠቀሜታው እንዲሁም ሌሎችም ተዛማጅ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ሰፊና አሳታፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም የስልጠናው አጠቃላይ ሂደት ጥሩ እንደነበር በማመስገን የገለጹት ተሳታፊዎቹ ለተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ናቸው፡፡
ጥቅምት 21/2018
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.