የሙስና ወንጀልን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ።

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሙስና ወንጀልን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያቤት እና ፍትህ ቢሮ በመተባበር  በዋና ኦዲተር መስሪያቤት ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።ሙስናን መታገል ለዋና ኦዲተር መስሪያቤት ዋና ተግባራችን ነው ያሉት የዋና ኦዲተር መስሪያቤት ኃላፊ አቶ አመንቴ መቻሉ ሲሆኑ የፀረሙስና ቀንን ማክበር ድርብ ተልዕኮአችን ነው ብለዋል።ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ረቂቅ ምርምር እና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና አጉራዊ  የጸረሙስና ኮንቬንሽን በመቀበል በርካታ ስራዎችን ሰርታለች ብለዋል።ዳሬክተሩ የሙስና ወንጀል አዋጁን አስመልክቶ በተለይ በስራ  አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል በዚህም ያለአግባብ ጉዳይ ማጓት ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊቶችን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ አክለው ስልጠናውን  ሰመጥተዋል።በማጠቃለያው የዋና ኦዲተር መስሪያቤት ኃላፊ አቶ አመንቴ መቻሉ የሕግ ረቂቅ ምርምር እና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል ሳላህ ለተነሱ ሃሳብ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.