ተግዳሮቶችን በመቋቋም የኤች አይቪ/ኤድስ ምላሽን በዘላቂነት እናረጋግጥ! በሚል መሪ ቃል የፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ ቀን ተከበረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ በሃገራችንና በከተማችን ለ36ኛ ጊዜ የየፀረ-ኤች አይቪ/ኤድስ ቀን የፍትሕ ቢሮ ዳይሬክተሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ በፍቃዱ የዕለቱን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ዜጎች ስለ ኤችአይቪ/ኤድስ ያላቸውን ግንዛቤ ይበልጥ እንዲያሳድጉ እና ወረርሽኙን በመከላከል ዙሪያ ሁሌም ንቁ ሆነው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም በሃገራችን የኤችአይቪ/ኤድስ መረጃዎች እና ስርጭቱን በማቅረብ በሽታው አሁንም በስፋት እየተስተዋለ እንደሚገኝ በማንሳት የመንግስት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ቤተሰብ ፣ የሚዲያ ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራዎችን የራሳቸው አጀንዳ አድርገው ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠርና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱት ሃሳብና አስተያየት አቶ ሲሳይ በፍቃዱ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡
ህዳር 22/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.