መልካም አስተዳደር የአንድ ሀገር ህልውና መሰረት እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የመልካም አስተዳደር ጽንሰ ሃሳብ ፣ ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስነ-ስርዓት በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ስልጠና ላይ ነው፡፡በስልጠናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ ጨምሮ፣ የክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ዳይሬክተሮች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም የሲቪክ ማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ መልካም አስተዳደር አመራሩና ሰራተኛው ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሆነ በመግለጽ መልካም አስተዳደር በየደረጃው ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ሰው ሃይል ከማብቃት፣ምቹ የስራ ቦታ አንጻር ከመደራጀት የማስፈጸም አቅምን ማረጋገጥ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ኃላፊው አክለውም መልካም አስተዳደር የአንድ ሀገር ህልውና መሰረት እንደሆነ ገልጸው አገልግሎት ለማግኘት የሚመጡ ተገልጋዮችን በግልጽነትና ተጠያቂነት በአግባቡ ማስተናገድ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ስልጠናውን የሰጡት ከከንቲባ ጽ/ቤት በመጡ አቶ ዋሲሁን በላይ ሲሆኑ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ሊኖር እንደሚገባ በመግለጽ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት፣ የህግ የበላይነት ሲሟላ መልካም አስተዳደር እንደሚሰፍን ገልጸዋል፡፡በስልጠናው የመልካም አስተዳደር ምንነት፣ የመልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ፣ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች እና መለያ መስፈርቶች ፣ የተለያዩ ሃገራት መልካም አስተዳደር በማስፈን ረገድ ያላቸው ተሞክሮ እንዲሁም የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስነ-ስርዓት በሚሉ ይዘቶች ላይ በስልጠናው ተካሄዷል፡፡በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት በማንሳት አቶ ዋሲሁን በላይ ምላሽ ሰጥተውበት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
ህዳር 24/2018
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.