በፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር...

image description
- ውስጥ Laws    0

በፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ዙርያ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

ስልጠናው የተሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በጋራ በመተባበር በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የተቋማት አመራሮችና ዳይሬክተሮች በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዐቃቢ ሕግ ብርሃን ደመቀ ሲሆኑ በፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ዙርያ ስለ የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ ስነ-ስርዓት ታሪካዊ ሂደት ፣ ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ ምንነትና መርሆች፣ ስለ የአስተዳደር መመሪያዎችና ውሳኔዎች የፍርድ ቤት ክለሳ ስነ-ስርዓት ፣ ስለ የመመሪያ አወጣጥ ስነ-ስርዓት እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ርዕሶች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ሰጥተዋል፡፡በዕለቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳብ አስተያየት የተነሱ ሲሆን ዐቃቢ ሕጓ ምላሽ ሰጥተው ስልጠናው በቀጣይ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናቶች እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

16/04/2018  


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.