የዓድዋ እሴት ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ማንሰራራት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ እና የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን የዓድዋ ድል በዓልን በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡በውይይቱም የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አስፋው ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የአድዋ ድል መላው የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት መገለጫ ነው ሲባል አባቶቻችን የሕይወትና የደም ዋጋ ከፍለው ነው ዛሬ በኩራት እንድንኖር ያስቻሉን ነው ብለዋል።ኃላፊው አክለው ይሄ ድል ሲመጣ በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ሳይከፋፈሉ ምንም አመቺ ሁኔታ ሳይኖር ይህንን ጀብድ ሰርተው ዘላለማዊ ክብር አጎናጽፈውን አልፈዋል ብለዋል።እኛ ዛሬ ከአባቶቻችን ምንማረው ወደኋላ በቀረንባቸው መስኮች ላይ በአይበገሬነት ፣ በጽናት በመስራት በታሪክ ተሰንዶ የሚኖር ለትውልድ የሚበጅ ስራ ሰርተን ማለፍ ነውም ብለዋል። የውይይቱ ሰነድ የዓድዋ አደራ አንድነት፣ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት በሚል ርዕስ በዋናነት ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል ፣ የዓድዋ ድል እንደ ብሔራዊ አንድነት እና የአሸናፊነት ምልክት ፣ ዓድዋ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ፣ የዓድዋ መንፈስ ለሁለንተናዊ የኢትዮጵያ ብልጽግና ፣ የዓድዋ ድል ተምሳሌትነት ለተግባራዊ የከተማ ብልጽግናችን መስፈንጠሪያ ፣ ዲሞክራሲያዊ ፅናት እና ፍትሃዊ ምርጫ በዓድዋ ዕይታ ፣ የዓድዋ አደራ የተቀበለው የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችን ዋስትና ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከአሁኑ ትውልድ ምን ይጠበቃል በሚሉ ርዕሶች በንባብ በመቅረብ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ባነሱት ሃሳቦች የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አስፋው እና የፍትሕ ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ በማወያየት ተጠናቋል፡፡
የካቲት11/2018
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.