የሕጻናትን ሰብዓዊ መብት ያረጋገጠ የፍትሕ ስርዓ...

image description
- ውስጥ Laws    0

የሕጻናትን ሰብዓዊ መብት ያረጋገጠ የፍትሕ ስርዓት ለመዘርጋት ማሕበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት ማጠናከር አስፈላጊ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ሆፕ ፎር ጀስቲስ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ማሕበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት ለሕጻናት ፍትሕ ማግኘት ባለው ፋይዳ ላይ ፖናል ውይይት አድርጓል።የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የፓናል ውይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት ሰዎች በሕግ ፊት እኩል የመታየት እና የመዳኘት ሕገ መንግስታዊ ጥበቃ አላቸው በማለት  ሕጻናት ፣ ሴቶች፣አካል ጉዳት ያለባቸው እና አረጋዊያን ልዩ ጥበቃና ከለላ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ሕገመንግስቱን ጨምሮ በበርካታ ሕጎች ተደንግጎ እናገኛለን ብለዋል ።ኃላፊው አክለው መንግስት የሕጻናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ብሎም ሕጻናት መብቶች አካታችነት ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ  የልማት ስራዎች በመስራት እመርታዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛልም ብለዋል።ወይዘሮ ሶስና ይርጋ የሆፕ ፎር ጀስቲስ ካንትሪ ዳይሬክተር ተቋማቸው በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና በዘመናዊ ባርነት ዙሪያ ትልልቅ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ገልጸው ከአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ጋር የሕጻናትን ጥቃት  ለመቀነስ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መስራታቸውን ዛሬ ደግሞ ማህበራዊ ፍትሕ አገልግሎት በዚህ ረገድ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ታምኖበት ፓናል ውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል። በወቅቱ አምስት ፓናልስቶች የመወያያ መነሻ ሀሳብ ያቀረቡ  ሲሆን የተለያዩ ሐሳብ አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል።በመጨረሻም ለተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለንቃተ ሕግ ስራ ሚኒ ሚዲያ አገልግሎት ለማደራጀት የሚውሉ ቁሳቁሶች ለትምህርት ቤቶቹ በስጦታ ከሆፕ ፎር ጀስቲስ ተበርክቷል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.