በወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር ዙሪያ ለፍትህ...

image description
- ውስጥ Laws    0

በወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር ዙሪያ ለፍትህ አካላት ስልጠና ተሰጠ ።

በወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር ዙሪያ ለፍትህ አካላት ስልጠና ተሰጠ ።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ፣ ተጠያቂዎችን ለህግ ለማቅረብ እና ለወንጀሉ ሰለባ የሆኑ ህፃናትና  ተጎጂዎችን መብት ጥበቃ ለማጠናከር  የፍትህ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በየጊዜው በህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች ዙሪያ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች  መጠናከር እንዳለባቸው በአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ የትብብር ጥምረት  ጽ/ቤት ኃላፊ  የሆኑት አቶ ዮሐንስ ብርሃኑ ገለፁ ።  በሰው የመነገድ ፣ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና  ሰውን በህገወጥ መንገድ ለሥራ ወደ ውጪ አገር የመላክ ወንጀሎች በዜጎች ሕይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በመሆናቸው የበለጠ ትኩረት ይሻሉ ። በመሆኑም ስለ ወንጀሎቹ ግንዛቤን ከመፍጠር ጀምሮ እስከ ማስቀጣት ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ የፖሊስ ፣ የአቃቢያነ ህግ እና የፍርድ ቤት ሚና የማይተካ ነው ብለዋል ኃላፊው ። ስልጠናው በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 ፣ በኢትዮጵያ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011፣የምስክሮች ጥበቃ አዋጅ 699/2003 እና በተጎጅዎች ጥበቃ ዙሪያ ነው ።መድረኩ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት  ከሲቪኤም ኢትዮጲያ ከተባለ ግብረ ስናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ተሳታፊዎች የተቋማትን ቅንጅት ለማጠናከር፣ የመረጃ ልውውጥን ለማሻሻል፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የግንዛቤ ሥራዎችን ለማስፋፋት እና ወንጀሉን የሚፈጽሙ ግለሰቦችን በህግ ፊት ለማቅረብና በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

ፍትህ ቢሮ ሰኔ 13  ቀን 2018 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.