''''የኢትዮጵያ ማንሰራራት''

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

''''የኢትዮጵያ ማንሰራራት''

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የሕብር ቀንን “ፍትሕ የኅብር መሠረት፤ እኩልነት የሰላም መሠረት፤ የሕግ የበላይነት የጋራ አብሮነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል በድምቀት አክብሯልበወቅቱ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች አስታራቂ ባህል አባቶች፣ አባ ገዳዎች ፣ ሃዴሲንቄዎች ፣ የጋሞ ባይራ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል ።እለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ ፍትሕ፣ የሕግ የበላይነትን፣ የዜጎችን መብትና ሰላማዊ የግጭት አፈታትን የሚያስፋፋ ተቋም በማለት፤ኃላፊው የፍትህ ስርዓቱ ተደራሽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የፍትህ አገልግሎትን ከመደበኛ ፍትህ አሰጣጥ ጋር በማቀናጀት ፍትህ አሰጣጥ ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነውም ብለዋል።ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ መፍታት ያለው ጠቀሜታ ፍርድ ቤቶች በቀላሉ በማህበረሰቡ ነባር እውቀቶች በሚፈቱ ጉዳዮች እንዳይጨናነቁ ከማድረግ ባሻገር ዜጎች ወጪያቸውን እና ጊዜያቸውን እንዳይባክን የሚያደርግ ዘዴ ነው ያሉት የፓናል ሰነድ አቅራቢ ታደሰ ስሜ (ዶ/ር) ናቸው።ርዕሰ ጉዳዩ ማዕከል ያደረገ በማድረግ ከፍትህ ሚንስቴር እና ከፍትህ ቢሮ በተገኙ ፓናልስቶች ሰፊ ማብራሪያ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።የውይይቱ ተሳታፊዎች ግጭቶች በባህላዊ መንገድ ሲፈቱ አንዱ አሸናፊ ሌላው ተሸናፊ አይሆኑም በሚል መንግስ መሰል አማራጭ ዘዴዎችን ማየትና ማስፋፋት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።

ጳጉሜ 4/2018

ፍትህ ቢሮ

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.