ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓሎቻችን ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን እንደሚያጠናክሩ ተገለፀ ።
ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓሎቻችን ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን እንደሚያጠናክሩ ተገለፀ ።
መስከረም 5/2019 ዓ.ም
ፍትህ ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ በቅርብ ቀን የሚከበሩትን የአደባባይ በዓላት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበር ከፍትህ ቢሮ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ከታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የፓናል ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደጀኔ እንዳሉት ኢትዮጵያ የብዙ ባህልና ሃይማኖታዊ እሴትና የትውፊት ባለቤት እንደመሆኗ ከበዓላቶቿ አንዱ በመስከረም ወር ውስጥ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት የመስቀል ዳመራ እና የእሬቻ በዓል ነው በማለት በዓላቶቹ በማይዳሰሱ ቅርሶች በዩኔስኮ የተመዘገቡና ቱሪስቶች ወደ ሀገራችን የሚመጡበት ፣ የሀገራችንን ከፍታና ሰላም እንደሆነች የምናሳይበት በዓል ነው ብለዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለውም ኢትዮጵያውያን የበርካታ ዘመናት የጋራ እሴቶች፣ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት መገለጫዎች የሆኑት እነዚህ በዓላት ያለምንም እንከን እና በሰላም እንዲጠናቀቁ ከመንግስት ሰራተኛው እንዲሁም ከሁሉም ማህበረሰብ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የፓናል ውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የፍትህ ቢሮ የወንጀል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሴ አንበሴ ናቸው።
የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ ወርቁ በበኩላቸው በዓላቱ ካላቸው የኢኮኖሚ ፋይዳ አንጻር ትልቅ በመሆኑ የህዝቦችን አንድነት እና ወንድማማችነት ይበልጥ በሚያጠናክር መልኩ እንዲከናወኑ እንዲሁም የእንግዳ ተቀባይነት ባህላችንን ባከበረ መልኩ ያለምንም የጸጥታ ችግር ሀይማኖታዊና ባሕላዊ ስርዓታቸውን ጠብቀው ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ ጸጥታዋ እና ልማቷ የተረጋገጠ ከተማ እንደመሆኗ በዓላቶቹ በሚከበሩበት ሰዓት ልማቶች እንዳይበላሹና እንዳይወድሙ መጠበቅ እንደሚገባና የህዝብን አንድነት ለማደፍረስ የሚጣሩ አካላትን የማክሸፍ ስራዎች መስራት እንደሚገባ የገለጹት የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በሀይሉ ክብረት ናቸው።
በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየታቸውን ሰጥተው ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.