"በማይመች ሁኔታ ውስጥ የሚያልፉ ሕፃናትን መታደ...

image description
- ውስጥ Laws    0

"በማይመች ሁኔታ ውስጥ የሚያልፉ ሕፃናትን መታደግ የሁሉም ግዴታ ነው!"

ይህ የተገለጸው በፍትሕ ቢሮ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሴቭ ዘ ችልድረን ጋር በመተባበር በህጻናት መብት ዙሪያ ለፖሊስ አመራሮች ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው።

በማይመች ሁኔታ ውስጥ የሚያልፉ ሕፃናትን መታደግ የሁሉም ግዴታ ነው ያሉት የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ሲሆኑ  ቤተሰብ እና ሃገር ትኩረት ያልሰጠው ታዳጊ ልጅ ለሃገር መፍትሔ አድርጎ መጠበቅ ባልዘሩበት ፍሬ መጠበቅ ነው ብለዋል።

ኃላፊው ከተማ አስተዳደሩ ታዳጊዎች ሀገር ገንቢ እና ተቆርቋሪ ዜጋ ለማድረግ ኮሪደር ልማቱን ተከትሎ መወያ፣ መዝነኛ ስፍራዎች ቀጣዩን ትውል ታሳቢ ያደረጉ ተግባራቶች ታዳጊ ህፃናትን ማዕከል ያደረገ ብሎም ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ ወጣት ጥፋተኞች  የሚታረሙበት ማገገሚያ ማዕከልም ለብቻ መኖሩ ተጨባጭ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።   

በሌላ በኩል ህፃናት ከጽንስ ጀምሮ ትኩረት አግኝተው  እንዲያድጉ የሚያስገድድ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራሞች  በህግ በሕግ ተደግፎ በተጨባጭ ችግር ፈቺ እየሆነ መምጣቱን አስታውሰዋል።

በፍትሕ ቢሮ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አጥናፉ ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ዘርፍ ለውጥ እያመጣ በመሆኑ እኛም የሚመጥን ስራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የማስተባበሪያው ኃላፊ አክለው ሰብዓዊ መብት ማንኛውም ሰው በተፈጥሮ የሚያገኘው መብት በመሆኑ ሊጣስ አይገባም ብለው ለዚህ ደግሞ የፖሊስ አካላት ሚናቸው የጎላ በመሆኑ አብረን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

  በወቅቱ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የፍታብሔር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ናሆም ሰለሞን  በህፃናት መብት ዙሪያ ሕጉ ምን ይላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ የተለያዩ ማጣቀሻዎችን አክለው ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.