እንኳን ለ1446ኛው የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለ1446ኛው የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በዓል አደረሳችሁ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ  በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች  የተቋማት አደረጃጀትና አሰራር ችግር ፈቺ፣ ቀልጣፋና ተዓማንነትን ያተረፈ እንዲሆን የህግ ማዕቀፎችን በጥናት ተመርኩዞ በማዘጋጀት፣ የጸደቁትን ተደራሽ በማድረግ፣ በሕግ ጉዳዮች የአስተዳደሩ ተቋማት ወኪልና አማካሪ በመሆን የህዝብ እና የመንግስትን መብትና ጥቅም ማስከበር ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ 

በመሆኑም  መላው ነዋሪ ውስን የሕዝብ ሀብት ተጠብቆ ለሀገር ልማት እንዲውል፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ነዋሪዎቻችን ከጎናችን ትሆኑ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን፡፡   

በዓሉን ስናከብር አንዳችን ለሌላችን ፍቅር በመስጠት፣ በመዋደድ፣ በመከባበር፣ በመተዛዘን እንዲሆን ይገባል ፡፡ 

በድጋሚ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል እንዲሆን በቢሯችን ስም ከልብ እመኛለሁ፡፡

                      ተክሌ በዛብህ

            የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 

               የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ

         ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.