
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሰዎች መነግድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በሰዎች መነግድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከልና መቆጣጠር ምክር ቤት ከክ/ከተማና ወረዳ አመራር ፣ከትብብር ጥምረት ም/ቤት፣ ከፀጥታ አካላት አንዲሁም ጥሪ ከተደረገላቸው ነዋሪዎች ጋር ሶስተኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
መድረኩን የመሩት የምክር ቤቱ ሰብሳቢና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ በሰዎች መነግድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተመሠረተው የትብብር ጥምረት ምክር ቤቱ ህዝቡ የጣለበችሁን ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ መተግበር እና በወንጀሉ ሰለባ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለወጭ ሀገር ሥራ የሚደልልን ደላላ ማጋለጥና ለሚመለከተው የፀጥታ አካላት መጠቆምና ተጠያቂ እንዲሆን መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሮቤል ኡርጌሳ በበኩላቸው በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን የመከላከልና የመቆጣጠር አሠራርና አፈጻጸም ዙሪያ የተዘጋጀውን ሰነድ ለተሳታፍዎች በስፈትና በዝርዝር አቅርበዋል ።
በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተከላካይ መቆጣጠር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ብርሃኑ በበኩላቸው የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና መቆጣጠር የሚቻለው የሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎና ኃላፊነት ሚና መወጣት ለትብብር ጥምረት ም/ቤቱ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ በመሆኑ አስቀድሞ ለመከላከልና ለነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ በመስጠት እና በወንጀል ተግባር ውስጥ ተዋናይ የሆኑ ተቋማትና ግለሰቦችን በወጣው አወጅ መሠረት ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል ።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰጠውን የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ለሥራዎቻችን መሳካት ሁነኛ መፍትሔ የሚያበረክት በመሆኑ በጋራ ጠንክረን እንሠራለን ሲሉ ተናግረዋል ።
ግንቦት 28-2017ዓ/ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.