ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 187_2017_የአመራር_አካዳሚ_የአደረጀጃትና_አሰራርን_ለመወሰን_የወጣ_ደንብ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ የሥራ መሪዎችና ባለሙያዎችን ዘመኑ የደረሰበት የብቃት ደረጃ ለማድረስ እና ሃገር በቀል የአመራር ዕውቀት፣ ክህሎትና ሥነ-ምግባር ችሎታቸውን በማነጽ የከተማውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ተልዕኮ መፈጸምና ማስፈጸም የሚችል አመራርና ባለሙያ እንዲኖር ለማድረግ፤ አካዳሚው የተቋቋመመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ አስፈላጊው የሙያና የአስተዳደር ነፃነት ያለው እና የአመራር እና የባለሙያ ሥልጠና፣ ጥናትና ምርምር፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ፣ የማማከርና የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥበትን የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ በአንቀጽ ፺፬ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡