ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 189/2017 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አስተዳደርን ለመወሰን የወጣ ደንብ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በሚኖርበት፣ በሚማርበት፣ በሚሰራበት አካባቢ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ለዚህም ዓላማ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲስፋፉና እንዲጠበቁ ማድረግ በማስፈለጉ፤የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በየአካባቢው በብዛትና በጥራት መኖርና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት የነዋሪውን በተለይም የወጣቱን ጤንነት ለመጠበቅ፣ አካል ለመገንባት፣ አዕምሮ በማበልጸግ ለሃገር እድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ለማስቻልና ስፖርቱ ለታለመለት ዓላማና ግብ እንዲውል ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቋቋሙበትን፣ የሚተዳደሩበትን፣ ቁጥጥር የሚደረግበትን እና ሕጋዊ ጥበቃ የሚያገኙበትን ግልፅ፣ ውጤታማ፣ የተቀናጀና ተጠያቂነት ያለበት ተቋማዊ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡