ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 190/2017 የምግብ ሥርዓት እና ኒውትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ደንብ

image description

በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ እና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂ እና የሰቆጣ ቃልኪዳን ፍኖተ ካርታ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በተሟላ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚመራ፣ የሚያቀናጅ እና የሚያስተባብር የሥርዓተ ምግብ እና ኒውትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋም በማስፈለጉ፤ የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸው የትምህርት ቤት ምገባ፣ የቀዳማዊ ልጅነት እና የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ሥራዎችን ከሀገር አቀፍ የምግብ ሥርዓት እና ኒውትሪሽን ፕሮግራሞች ጋር በማስተሳሰር አስፈጻሚ ተቋማት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በማሳደግ ወደ ተግባር ማስገባት የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፪ መስረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡